ስለምልጃ ( ክፍል ሁለት )

ይህን ክፍል ከማጠቃለላችን በፊት በኤርምያስ 421-6 ያለውን ቃል እንመልከት። ሕዝቡ ወደ ነብዩ ኤርምያስ ቀርበው «…ዓይኖችህ እንዳዩን ከብዙ ጥቂት ቀርተናልና ልመናችን፥ እባክህ፥ በፊትህ ትድረስ፤ አምላክህም እግዚአብሔር የምንሄድበትን መንገድና የምናደርገውን ነገር ያሳየን ዘንድ ስለ እኛ፥ ስለዚህ ቅሬታ ሁሉ፥ ወደ አምላክህ ወደ እግዚአብሔር ጸልይ አሉት» ኤርምያስም መልሶ እንዲህ አላቸው፡- «…ሰምቻችኋለሁ፤ እነሆ፥ እንደ ቃላችሁ ወደ አምላካችሁ ወደ እግዚአብሔር እጸልያለሁ፤ እግዚአብሔርም የሚመልስላችሁን ሁሉ እነግራችኋለሁ፥ ከእናንተም ምንም አልሸሽግም አላቸው።» እነርሱም መልሰው «…አምላክህ እግዚአብሔር በአንተ እጅ ወደ እኛ የላከውን ነገር ሁሉ ባናደርግ፥ እግዚአብሔር በመካከላችን እውነተኛና ታማኝ ምስክር ይሁን። የአምላካችንን የእግዚአብሔርን ቃል በመስማታችን መልካም እንዲሆንልን፥ መልካም ወይም ክፉ ቢሆን፥ አንተን ወደ እርሱ የምንልክህ የአምላካችንን የእግዚአብሔርን ቃል እንሰማለን አሉት።»
ይህ ግልጽ ትምህርት እንዲህ ባለ መልኩ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተጽፎ መገኝቱን ከተመለከትን ትኩረት ሰጥተን ልናስብበት የሚገባን ነጥብ ነቢዩ ኤርምያስ በምድር ላይ በኖረበት ዘመን የምልጃ አገልግሎት መስጠት መቻሉና የእስራኤልም ልጆች ይህንን ተረድተው ወደ አምላካቸው ነቢዩን መላካቸው አብሮአቸው ይኖር ስለነበር መሆኑንና ነቢዩ ከሞተ በኋላ ግን ከእስራኤል ልጆች ማንም በየትኛውም ዘመንና ሥፍራ ለምልጃ አገልግሎት ኤርምያስን ሲጠራ ይልተሰማ መሆኑን ነው። ቢደረግም ከንቱ ድካም ብቻ ሆኖ መቅረቱን ነው።
በመጨረሻም ደመቅ ተደርጎ ሊሰመርበት የሚገባው ነጥብ ከላይ የተመለከትናቸው ሰዎች ሁሉ በምድር በኖሩበት ዘመን ስለ ሌሎች ይማልዱ እንደነበር እንጂ ከዚህ ዓለም በሞት ከተለዩ በኋላ የምልጃ አገልግሎት ይቀጥላሉ ብሎ መገመትም ሆነ እንዲህ የሚልን ትምህርት መቀበል መጽሐፍ ቅዱስ የማይደግፈውና የሰው ሥርዓትና ትምህርት ብቻ መሆኑን ነው።
አንድን ሰው የትምህርት እድል እንዲያገኝ መጣር ተገቢ ሆኖ ሳል ምንም ሳይማር ወይም በቂ እውቀት ሳይኖረው ከክፍል ወደ ክፍል እንዲዛወር ለማገዝ መሞከር ልክ እንዳልሆነ ሁሉ፣ አንዱ ስለሌላው መማለድ ቃለ እግዚአብሔር የሚደግፈው ሆኖ ሳለ ነገር ግን በጸሎት ብዛት የእግዚአብሔርን ቃል ሳይታዘዝ መንግሥተ ሰማያትን እንዲወርስ ለማድረግ መሞከር ስሕተት ነው።
2. ሰው ከሞተ በኋላ ያማልዳልን?
የሰው ትምህርትና ሃሳብ ካልሆነ በስተቀር ክቡርና ሕያው በሆነው በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ በብሉይ ኪዳንም ሆነ በአዲስ ኪዳን በአንድም ቦታ የሞቱ ሰዎች ለአማላጅነት ሲጠሩ አይታዩም፡፡ ስለዚህ «ሰው ከሞተ በኋላ ያማልዳል» የሚል ትምህርት መጽሐፍ ቅዱሳዊ አይደለም፡፡ ከጻድቃን ሆነ ከሰማዕታት አንዳቸውም ከሞቱ በኋላ «አማልዱን» ሲባሉ ወይም ደግሞ ሲማልዱ አልታዩም፤ አልተሰሙም፤ በቅዱስ ቃሉ ውስጥ ከቶ አልተጻፈምም፡፡
የሞቱ ሰዎች በሕይወት ያሉትን በጸሎት ሊረዱ ይቅርና በሉቃስ 1626-31 እንደተጻፈው «ከዚህም ሁሉ ጋር ከዚህ ወደ እናንተ ሊያልፉ የሚፈልጉ እንዳይችሉ፣ ወዲያ ያሉ ደግሞ ወደ እኛ እንዳይሻገሩ በእኛና በእናንተ መካከል ታላቅ ገደል ተደርጎአል…» ብሎ አብርሃም እንደመለሰና ሃብታሙ ሰውዬም «እንኪያስ፣ አባት ሆይ፣ (ዓልዓዛርን) ወደ አባቴ ቤት እንድትሰደው እለምንሃለሁ፤ አምስት ወንድሞች አሉኝና፤ እነርሱ ደግሞ ወደዚህ ሥቃይ ስፍራ እንዳይመጡ ይመስክርላቸው» እንዳለው እናነባለን፡፡ ይበል እንጂ አሁን ባለንበት ዓለምና በወዲያኛው ዓለም ባሉ ሰዎች መካከል ምንም ግንኙነት እንደሌለ ሲያመለክት አብርሃምም መልሶ፡- «…ሙሴና ነቢያት አሉአቸው፤ እነርሱን ይስሙ አለው፡፡ እርሱም፡- አይደለም፣ አብርሃም አባት ሆይ፣ ነገር ግን ከሙታን አንዱ ቢሄድላቸው ንስሐ ይገባሉ አለ፡፡» አብርሃም ግን መልሶ «ሙሴንና ነቢያትንም የማይሰሙ ከሆነ፣ ከሙታንም እንኳ አንድ ቢነሣ አያምኑም አለው፡፡» «ሙሴና ነቢያት» ሲል የሙሴ ሕግና የነቢያት መጽሐፍትን ለማመልከት ነው፡፡ የሞተ ሰው ምንም ጻድቅ ቢሆን በዚህ ምድር የሚካሄደውን አንዳች ነገር ስንኳን አያውቅም፡፡ ድርሻና ዕድል ፈንታም የለውም፡፡
አብርሃም መጽሐፍ ቅዱስ የመሰከረለት ጻድቅ ሰው ሆኖ ሳለ እርሱም ሆነ የልጅ ልጁ ያዕቆብ (እስራኤል) ከሞቱ በኋላ በሥጋ ልጆቻቸው ስለሆኑት ስለ እስራኤላውያን ምንም እንደማያውቁ የእግዚአብሔር ቃል ሲናገር «አብርሃም ባያውቀን እስራኤልም ባይገነዘበን አንተ አባታችን ነህ፤ አቤቱ፣ አንተ አባታችን ነህ፣ ስምህም ከዘላለም ታዳጊያችን ነው» (ኢሳይያስ 6316) ይላል፡፡ ሰሎሞንም «ያልሞተ ውሻ ከሞተ አንበሳ ይሻላልና ሰው ከሕያዋን ሁሉ ጋር በአንድነት ቢኖር ተስፋ አለው፡፡ ሕያዋን (ያልሞቱ በምድር ያሉ) እንዲሞቱ ያውቃሉና፤ ሙታን ግን አንዳች አያውቁም፤ መታሰቢያቸውም ተረስቶአልና ከዚያ በኋላ ዋጋ የላቸውም፡፡ ፍቅራቸውና ጥላቸው ቅንዓታቸውም በአንድነት ጠፍቶአል፣ ከፀሐይ በታችም በሚሠራው ነገር ለዘላለም እድል ፈንታ ከእንግዲህ ወዲህ የላቸውም» (መክብብ 94-6) ብሎአል፡፡
ሐጌና ዘካርያስም በመዝሙራቸው «ማዳን በማይችሉ በሰው ልጆችና በአለቆች አትታመኑ፡፡ ነፍሱ ትወጣለች ወደ መሬቱም ይመለሳል፤ ያን ጊዜ ምክሩ ሁሉ ይጠፋል» (መዝሙር 1463-4) ብለዋል፡፡ ጻድቅ መሆኑ የተመሰከረለት ኢዮብም «አሁንም ጥራ፤ የሚመልስልህ አለን? ከቅዱሳንስ ወደማናቸው ትዞራለህይላል (ኢዮብ 51)
በመዝሙር 8810-13 ደግሞ እንዲህ የሚል ቃል እናገኛለን፦ «በውኑ ለሙታን ተኣምራት ታደርጋለህን? የሞቱትስ ተነሥተው ያመሰግኑሃልን? በመቃብርስ ውስጥ ቸርነትህን፥ እውነትህንስ በጥፋት ስፍራ ይናገራሉን? ተአምራትህ በጨለማ፥ ጽድቅህንም በመርሳት ምድር ትታወቃለችን? አቤቱ፥ እኔ ግን ወደ አንተ ጮኽሁ፤ በጥዋት ጸሎቴ ወደ ፊትህ ትደርሳለች።»
ይህ ሲባል የእምነት ጀግኖች የነበሩ ቅዱሳን ነገር ግን አሁን በአጸደ-ሥጋ የሌሉ ለዚህኛው ዓለም የሚሠሩት ነገር የለም ለማለት እንጂ በአጸደ-ነፍስ በክብር በገነት ማረፋቸውን በመዘንጋት አይደለም፡፡ ከሞቱ ሰዎች ጋር ለመነጋገር መሞከር በሙታን ሳቢዎች እና በአጋንንት አሠራር ሽንገላ ለመታለል ራስን አሳልፎ ለመስጠት ካልሆነ በስተቀር መጽሐፍ ቅዱስ የማይደግፈው ከንቱ ጥረት መሆኑ ግልጽ ነው (1ሳሙኤል 288)
በኢሳይያስ 819-22 ያለው ሕያው ቃል ከላይ የተመለከትነውን እውነት የበለጠ ያጎላዋል እንዲህ በማለት፦
«እነርሱም፦ የሚጮኹትንና ድምፃቸውን ዝቅ አድርገው የሚናገሩትን መናፍስት ጠሪዎችንና ጠንቋዮችን ጠይቁ ባሉአችሁ ጊዜ፥ ሕዝቡ ከአምላኩ መጠየቅ አይገባውምን? ወይስ ለሕያዋን ሲሉ ሙታንን ይጠይቃሉን? ወደ ሕግና ወደ ምስክር ሂዱ! እንዲህም ያለውን ቃል ባይናገሩ ንጋት አይበራላቸውም። እነርሱም ተጨንቀውና ተርበው ያልፋሉ፤ በተራቡም ጊዜ ተቈጥተው ንጉሣቸውንና አምላካቸውን ይረግማሉ፥ ወደ ላይም ይመለከታሉ፤ ወደ ምድርም ይመለከታሉ፥ እነሆም፥ መከራና ጨለማ የሚያስጨንቅም ጭጋግ አለ፤ ወደ ድቅድቅም ጨለማ ይሰደዳሉ።»
እግዚአብሔር ባሪያዎቹ በአጸደ-ሥጋ በምድር እያሉ በእነርሱ የተናገረውን ቃል ከሞቱ በኋላም ይፈጽማል፡፡ ይህም እርሱ ሕያው ስለሆነ ሰማይና ምድር ቢያልፉም ቃሉ ስለማያልፍ ብቻ መሆኑ መዘንጋት የሌለበት ትልቅ ነጥብ ነው (2ነገሥት 1934 206 1320-21 ይመልከቱ)፡፡ በምድር ያሉ ሰዎች በሞት ከዚህ ዓለም የተለዩትን ቢጠሩአቸው ሊሰሙአቸው አይችሉም፡፡ የት ተገኝተው «አማልዱኝአማልደኝአማልጂኝ» ሊባሉ? በምድር ላይ ሲኖሩ በጊዜና በቦታ ውስን እንደነበሩ በሞት ሲለዩም እንዲሁ ናቸው፡፡ ለዚህም ቅዱስ ቃሉን ማሰላሰልና ትንሽ ቆም ብሎ ማሰብን ብሎም ማገናዘብን ይጠይቃል፡፡
የምንወዳቸው ወገኖቻችን በሞት በተለዩን ጊዜ ስማቸውን እየጠራን በቀጥታ ለእነርሱ እየተናገርን ማልቀሳችን ለራሳችን እንጂ ስለሚሰሙን አይደለም፡፡ የሉማ! ሄደዋላ! በዐጸደ-ነፍስ ያሉትን ቅዱሳንም መጥራት ከዚህ ምንም ልዩነት የለውም፡፡ ቅዱሳን ስለሞቱ ብቻ እንደ እግዚአብሔር በአንድ ጊዜ በሁሉ ሥፍራ መገኘት የሚችሉ የሚመስላቸው ሰዎች ይኖሩ ይሆናል፡፡ ነገር ግን በአንድ ጊዜ በሁሉ ሥፍራ መገኘት የፈጣሪ ባሕርይ ብቻ እና ችሎታ መሆኑ መዘንጋት የለበትም (መዝሙር 1397-10) የሞተ ኃጢአተኛ ደመኛውን ወደ ምድር ተመልሶ መበቀል እንደማይችል ሁሉ እንዲሁ የሞተ ጻድቅ ወደ ምድር ተመልሶ የጽድቅ ሥራውን ለማከናወን እንደማይችል ግልጽ የሚያደርገው ሐዋርያው ጳውሎስ ወደ ሞት በቀረበ ሰዓት እንዲህ ብሎአል «በመሥዋዕት እንደሚደረግ፥ የእኔ ሕይወት ይሠዋልና፥ የምሄድበትም ጊዜ ደርሶአል። መልካሙን ገድል ተጋድዬአለሁ፥ ሩጫውን ጨርሼአለሁ፥ ሃይማኖትን ጠብቄአለሁ፤ ወደ ፊት የጽድቅ አክሊል ተዘጋጅቶልኛል፥ ይህንም ጻድቅ ፈራጅ የሆነው ጌታ ያን ቀን ለእኔ ያስረክባል…» (2ጢሞቴዎስ 46-8) «ሩጫውን ጨርሼአለሁ»
2ጴጥሮስ 112-15 የምንመለከተውም ይህንኑ ነው፡፡ ሐዋርያው ጴጥሮስ ለቅዱሳን ያለመታከት መትጋትና መድከም ያለበት ከዚህ ዓለም ከተለየ በኋላ ሳይሆን በአፀደ-ሥጋ ሲኖር ብቻ መሆኑን ለማሳየት «ስለ እነዚህ ዘወትር እንዳሳስባችሁ ቸል አልልም፡፡ ሁልጊዜም በዚህ ማደሪያ ሳለሁ በማሳሰቤ ላነቃችሁ የሚገባኝ ይመስለኛል፤ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንዳመለከተኝ ከዚህ ማደሪያዬ መለየቴ ፈጥኖ እንዲሆን አውቃለሁና፡፡ ከመውጣቴም  በኋላ እነዚህን ነገሮች እንድታስቡ በየጊዜው ትችሉ ዘንድ እተጋለሁ» በማለት «እንዲህ ተናግሮን ነበር» እያላችሁ የተናገርኩትን ቃል እንድታስቡ ከመሞቴ በፊት አስፈላጊውን ሁሉ ላስተምራችሁ ቸል አልልም ብሎአል፡፡
የሞቱ ጻድቃን የት ነው የሚሄዱት? ከድካማቸው ወደሚያርፉበት ሥፍራ ይከማቻሉ (ራእይ 1413) እንጂ በዚህ ምድር ካሉ ሰዎች ጋር መነጋገር አይችሉም (ራእይ 69-11)፡፡ እንኳን ሞተው ይቅርና በምድር እያሉም በሃሳብ እንጂ ከእነርሱ ርቀው ካሉ ሰዎች ጋር መነጋገር ስለማይችሉ ሐዋርያው ጳውሎስ በቆላስይስ 25 «በመንፈስ ከእናንተ ጋር ነኝና፣ ሥርዓታችሁንም በክርስቶስም ያለውን የእምነታችሁን ጽናት እያየሁ ደስ ይለኛል» ብሎአል።
በአጠቃላይ ዕብራውያን 723-25 ሰው ከሞተ በኋላ እንደማያማልድ አጭርና ግልጽ መልስ ይሰጠናል። እንዲህ በማለትእነርሱም እንዳይኖሩ ሞት ስለ ከለከላቸው ካህናት የሆኑት ብዙ ናቸው፤ እርሱ ግን ለዘላለም የሚኖር ስለሆነ የማይለወጥ ክህነት አለው፤ ስለ እነርሱም ሊያማልድ ዘወትር በሕይወት ይኖራልና ስለዚህ ደግሞ በእርሱ ወደ እግዚአብሔር የሚመጡትን ፈጽሞ ሊያድናቸው ይችላል።ይህ የሆነው ሕያው ሆኖ ለዘላለም የሚኖር አማላጅም ተማላጅም አንድ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ስለሆነና እርሱ ብቻ ሞትን ድል ስላደረገ ነው (2ቆሮንቶስ 519-21 ኢሳይያስ 5915-17)
ሌሎችን ግን ሞት አሸነፋቸው። ማንንም የማያድኑ በጽድቃቸው ለራሳቸው እንጂ ለሌላ የማይተርፉም መሆናቸውን ለማስረዳት በሕዝቅኤል 1414 «እነዚህ ሦስት ሰዎች፥ ኖኅና ዳንኤል ኢዮብም፥ ቢኖሩባት በጽድቃቸው የገዛ ነፍሳቸውን ብቻ ያድናሉ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።» እንኳን ሞተው በምድር ላይ ቢኖሩም «እነዚህ ሦስት ሰዎች ቢኖሩባት፥ እኔ ሕያው ነኝና እነርሱ ብቻቸውን ይድናሉ እንጂ ወንዶችንና ሴቶች ልጆቻቸውን አያድኑም፥ ምድሪቱም ባድማ ትሆናለች፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር» (.16)
ስለዚህ እግዚአብሔር በቃሉ አጥብቆ እንደሚያስጠነቅቀንበሰው ከመታመን ይልቅ በእግዚአብሔር መታመን ይሻላል…” በማለት ነው (መዝሙር 1188-9 ኤርምያስ 175-8)
ክፍል አራት
የእጅ መንሻ ምልጃ
ይህ ምልጃ በገንዘብም ይሁን በተለያዩ ስጦታዎችና ጥቅማጥቅሞች አንድን ሰው ወይም ወገን ሕጋዊ ባልሆነ መንገድ አግባብቶ ፍርድ እንዲዛባ ጥረት ማድረግ ነው፡፡ ትክክለኛ ተግባር አከናውኖ ተገቢውን ዋጋ መቀበል ይገባል፡፡ ነገር ግን ይህ ሳይሆን ቀርቶ የበላይን በመደለል ተገቢ ያልሆነ ጥቅምን ለማግኘት መሞከር በሰዎች ዘንድ ቢኖርም ሕገወጥ ብቻ ሳይሆን ኃጢአትም ነው፡፡ ይህ ዓይነቱ ምልጃ በእግዚአብሔር ፊት አጸያፊ ነገር ስለሆነ እግዚአብሔር አይቀበለውም፡፡ «እንግዲህ አምላካችሁ እግዚአብሔር የአማልክት አምላክ የጌቶችም ጌታ፣ ታላቅ አምላክ ኃያልም የሚያስፈራም፣ በፍርድ የማያደላ፣ መማለጃም የማይቀበል ነውና እናንተ የልባችሁን ሸለፈት ግረዙ» ይላል (ዘዳግም 101617)፡፡
እግዚአብሔር በመስዋዕት /በስጦታ/ ብዛት አይደለልም፡፡ ሳኦል የታዘዘውን ሳያደርግ ቀርቶና በራሱ ፈቃድ ሄዶ ሲያበቃ ምናልባት የመስዋዕት ብዛት እግዚአብሔርን ያስደስት ይሆናል ብሎ በመገመት የእጅ መንሻ በማቅረብ ፍርድን ለማስቀየር ሲሞክር «በውኑ የእግዚአብሔርን ቃል በመስማት ደስ እንደሚለው እግዚአብሔር በሚቃጠልና በሚታረድ መሥዋዕት ደስ ይለዋልን? እነሆ፣ መታዘዝ ከመሥዋዕት፣ ማዳመጥም የአውራ በግ ስብ ከማቅረብ ይበልጣል፡፡ ዓመፀኝነት እንደ ምዋርተኛ ኃጢአት፣ እልከኝነትም ጣዖትንና ተራፊምን እንደ ማምለክ ነው፤ የእግዚአብሔርን ቃል ንቀሃልና እግዚአብሔር ንጉሥ እንዳትሆን ናቀህ…» ተባለ (1ሳሙ 1522-23)፡፡
ጥንትም ሆነ ዛሬም፣ ሰዎች ትክክለኛውንና የቀናውን መንገድ ትተው በመሰላቸው በመሄድ እግዚአብሔር ከኃጢአት ሁሉ ከሚያነጻበት መንገድ ወጥተው በመሳት እጅ መንሻ ይዘው ፈጣሪን ሊደልሉ ቢሞክሩ በኢሳይያስ 113-16 «ምናምንቴውን ቁርባን ጨምራችሁ አታምጡ፤ ዕጣን በእኔ ዘንድ አጸያፊ ነው፤ መባቻችሁንና ሰንበታችሁን በጉባኤ መሰብሰባችሁን አልወድድም፤ በደልንም የተቀደሰውንም ጉባኤ አልታገሥም፡፡ መባቻችሁንና በዓላቶቻችሁን ነፍሴ ጠልታለች፤ ሸክም ሆነውብኛል፣ ልታገሣቸውም ደክሜያለሁ፡፡ እጃችሁንም ወደ እኔ ብትዘረጉ ዓይኔን ከእናንተ እሰውራለሁ፣ ልመናንም ብታበዙ አልሰማችሁም፤ እጆቻችሁ ደም ተሞልተዋል፡፡ ታጠቡ ሰውነታችሁንም አንጹ፤ የሥራችሁን ክፋት ከዓይኔ ፊት አስወግዱ፤ ክፉ ማድረግን ተዉ፣» ይላል፡፡
ደግሞም «በሬን የሚያርድልኝ ሰውን እንደሚገድል ነው፤ ጠቦትንም የሚሠዋ የውሻውን አንገት እንደሚሰብር ነው፤ የእህልን ቁርባን የሚያቀርብ የእርያን ደም እንደሚያቀርብ ነው፤ ዕጣንን የሚያጥን ጣዖትን እንደሚባርክ ነው፡፡ እነዚህ የገዛ መንገዳቸውን መረጡ፤ ነፍሳቸውም በርኩሰታቸው ደስ ይላታል፤ እኔ ደግሞ የተሳለቀባቸውን እመርጣለሁ፣ የፈሩትንም ነገር አመጣባቸዋለሁ፤ በፊቴ ክፉ ነገርን አደረጉ፣ ያልወደድሁትንም መረጡ እንጂ በጠራሁ ጊዜ አልመለሱልኝምና፣ በተናገርሁም ጊዜ አልሰሙኝምና» (ኢሳይያስ 661-4) በማለት ሌላ አመጽ እንደ ጨመሩ ይነግራቸዋል እንጂ ከቶ አይሰማቸውም፡፡
እንዲህ ዓይነቱን ምልጃ የሚቀበሉ ሰዎችም በእግዚአብሔር ፊት የተጠሉ መሆናቸውን በሚክያስ 311 ሲናገር «አለቆችዋ በጉቦ ይፈርዳሉ፣ ካህኖቶችዋም በዋጋ ያስተምራሉ፣ ነቢያቶችዋም በገንዘብ ያምዋርታሉ፣ ከዚህም ጋር፡- እግዚአብሔር በመካከላችን አይደለምን? ክፉ ነገር ምንም አይመጣብንም እያሉ በእግዚአብሔር ይታመናሉ» ብሎአል (ሕዝቅኤል 138-19) በሐዋ. 818-24 ላይ የምናገኘው ሲሞን የተባለው ሰውም «በሐዋርያት እጅ መጫን መንፈስ ቅዱስ እንዲሰጥ ባየ ጊዜ፣ ገንዘብ አመጣላቸውና፡- እጄን የምጭንበት ሁሉ መንፈስ ቅዱስን ይቀበል ዘንድ ለእኔ ደግሞ ይህን ሥልጣን ስጡኝ አለ፡፡ ጴጥሮስ ግን እንዲህ አለው፡- የእግዚአብሔርን ስጦታ በገንዘብ እንድታገኝ አስበሃልና ብርህ ከአንተ ጋር ይጥፋ፡፡ ልብህ በእግዚአብሔር ፊት የቀና አይደለምና ከዚህ ነገር ዕድል ወይም ፈንታ የለህም» ብሎታል፡፡
ታዲያ እግዚብሔር ከሰው ምን ይፈልጋል? ብንል በሚክያስ 57-8 «ሰው ሆይ፣ መልካሙን ነግሮሃል፤ እግዚአብሔርም ከአንተ ዘንድ የሚሻው ምንድር ነው? ፍርድን ታደርግ ዘንድ፣ ምሕረትንም ትወድድ ዘንድ፣ ከአምላክህም ጋር በትሕትና ትሄድ ዘንድ አይደለምንበማለት ይመክረናል፡፡
ሰው ከሞተ በኋላ እግዚአብሔር በብዙ ድግስ ተደልሎ «ነፍሱን ሊምራት ወይም ከሲኦል ወደ መንግሥተ ሰማያት ሊያወጣት ይችላል» በሚል የተሳሳተ እውቀት የነፍስ-ይማር ድግስ ወይም ተዝካር የሚደግሱና የሚያስደግሱ የሚያበሉና የሚበሉ መጽሐፍ ቅዱሳዊ በሆነ መንገድ ላይ አለመሆናችውን ቅዱስ ቃሉ ያረጋግጥልናል። የነፍስ መዳን ወይም ደህንነት ወይም የዘላለም ሕይወት በድግስ፣ በመሥዋዕት ብዛትና በገንዘብ አይገዛም፡፡ ከኃጢአት የሚያነጻ የክርስቶስ ደም ብቻ ነው (1ዮሐንስ 17-10)፡፡ እውነተኛ አምላክና የዘላለምም ሕይወት እርሱ ብቻ ነው ሌላው ሁሉ ጣዖት ነው ይላል (1ዮሐንስ 52021)
በሞት ስለተለዩን ስለምንወዳቸው ወገኖቻችን ነፍስ ብለን እየደገስን ብናበላ፤ የበላ የጠጣም «ነፍስ ይማርወይም «መንግሥተ ሰማይን ያዋርስልንእያለ ቢመርቅ ተዝካር የደገስንላቸው የሞቱ ወገኖቻችን ነፍሳቸው ገና ያልተማረ መንግሥተ ሰማይንም ያልወረሱና በሲኦል ያሉ መሆናቸው እየታወቀ የማይጸናንና የማይፈጸምን ከንቱ ምኞት በድግስ ከማወጅ በስተቀር ምንም ፋይዳ የለውም፡፡ ቆም ብሎ ላሰበው ደግሶእወቁልኝ የሞተው ዘመዴ በሲኦል ነው ያለውከማለት በስተቀር ሌላ ትርጉምም ሆነ ጠቀሜታ የለውም።
ማንም ሰው መንግሥተ ሰማይ ለመግባት በአጸደ-ሥጋ ሳለ ዘዳግም 64-9 እና ማርቆስ 1229-32 አምኖ፤ በሕዝቅኤል 1820-32 በሉቃስ 131-9 መሠረት ንስሐ ገብቶ፤ በዮሐንስ 33-5 በሐዋ. 238-42 የተጻፈውን ሕያው ቃል ታዝዞና 1ተሰሎንቄ 523 እና በዕብራውያን 1214 መሠረት ጌታ ዳግም እስኪመጣ በቅድስና መኖር ይጠበቅበታል። ሰው ከሞተ በኋላ ግን ፍርድ እንጂ የንስሃ እድል እንደሌለው ዕብራውያን 927 ያስረዳል፡፡
ለተራበ ማብላት የተራቆተን ማልበስ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ተግባር ነው፡፡ ነገር ግን ከኃጢአት ሳይርቁ ደግሰው ቢያበሉ፣ ስጦታ ቢያበዙ በቅዱስ ቃሉ መሠረት ታዝዞ ነፍስን ከማዳን ጋር ካልሆነ ብቻውን አንዳች ጠብታ ጽድቅ የለውም፡፡ ያለጽድቅ የሚደረግ ሁሉ ዋጋ ቢስና ከንቱ ድካም ይሆናል፡፡
በማቴዎስ 1041 ላይ ያለውን ቃል ለራስ በመተርጎም በሞቱ ሰዎች ስም (ማንነታቸው ወይም ጽድቃቸው በእግዚአብሔር ቃል ይልተረጋገጠ) ደግሶ ማብላት የሚያጸድቃቸው እንደሆነ ተደርጎ የተነገራቸው በመጨረሻ አመድ አፋሽ ሆነው የቀሩና ዛሬም ካልተመለሱ ይህ ዕጣ የሚጠብቃቸው አያሌ ናቸው። ቃሉ እንዲህ ይላል፦ «እናንተን የሚቀበል እኔን ይቀበላል፥ እኔንም የሚቀበል የላከኝን ይቀበላል። ነቢይን በነቢይ ስም የሚቀበል የነቢይን ዋጋ ይወስዳል፥ ጻድቅንም በጻድቅ ስም የሚቀበል የጻድቁን ዋጋ ይወስዳል። ማንም ከእነዚህ ከታናናሾቹ ለአንዱ ቀዝቃዛ ጽዋ ውኃ ብቻ በደቀ መዝሙር ስም የሚያጠጣ፥ እውነት እላችኋለሁ፥ ዋጋው አይጠፋበትም።» ትርጉሙን ለመረዳት ሰውን መስማት ሳይሆን ማርቆስ 941 ማንበብ ተገቢ ነው። እንዲህ ይላል «የክርስቶስ ስለ ሆናችሁ በስሜ ጽዋ ውኃ የሚያጠጣችሁ ሁሉ፥ ዋጋው እንዳይጠፋበት እውነት እላችኋለሁ።» ማለት ምን ማለት እንደሆነ በተግባር የታዩ ምሳሌዎችን ስንመለከት፦
 1ነገሥት 179-24 የሰራኘታዋ ባልቴት ነቢዩ ኤልያስን እንደ ተቀበለችው ማለት ነው፤
    2ነገሥት 48-37 ሱነማዊቷ ሴት ነቢዩ ኤልሳዕን እንደ ተቀበለችው ማለት ነው፤
    በሐዋ. 1614-15 ልድያ እነሐዋርያው ጳውሎስን እንደተቀበለችው ማለት ነው፤
ነገር ግን በቅዱሳን መላእክትም ሆነ በሞቱ ሰዎች ስም ድግስ አዘጋጅቶ የጋበዘና ያበላ አንድ ሰው እንኳን በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የለም። ለቅዱስ ቃሉ ባዕድ የሆነ ሥራ አንሥራ!
ዕብራውያን 610 «እግዚአብሔር፥ ቅዱሳንን ስላገለገላችሁ እስከ አሁንም ስለምታገለግሉአቸው፥ ያደረጋችሁትን ሥራ ለስሙም ያሳያችሁትን ፍቅር ይረሳ ዘንድ ዓመፀኛ አይደለምና።» በመጨረሻ የነገሥታት ንጉሥ ሲገለጥ በማቴዎስ 25:33-40 እንደተጻፈ «በጎችን በቀኙ ፍየሎችንም በግራው ያቆማቸዋል። ንጉሡም በቀኙ ያሉትን እንዲህ ይላቸዋል፡- እናንተ የአባቴ ቡሩካን፥ ኑ፤ ዓለም ከተፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ የተዘጋጀላችሁን መንግሥት ውረሱ። ተርቤ አብልታችሁኛልና፥ ተጠምቼ አጠጥታችሁኛልና፥ እንግዳ ሆኜ ተቀብላችሁኛልና፥ ታርዤ አልብሳችሁኛልና፥ ታምሜ ጠይቃችሁኛልና፥ ታስሬ ወደ እኔ መጥታችኋልና። ጻድቃንም መልሰው ይሉታል፡- ጌታ ሆይ፥ ተርበህ አይተን መቼ አበላንህስ? ወይስ ተጠምተህ አይተን መቼ  አጠጣንህ? እንግዳ ሆነህስ አይተን መቼ ተቀበልንህ? ወይስ ታርዘህ አይተን መቼ አለበስንህ? ወይስ ታመህ ወይስ ታስረህ አይተን መቼ ወደ አንተ መጣን? ንጉሡም መልሶ፡- እውነት እላችኋለሁ፥ ከሁሉ ከሚያንሱ ከእነዚህ ወንድሞቼ ለአንዱ እንኳ ስላደረጋችሁት ለእኔ አደረጋችሁት ይላቸዋል።» እንደዚህ ከሚባልላቸው ዕጣ ክፍል ለመቆም ከተፈለገ ስማቸውን መጽሐፍ ቅዱስ የማያውቃቸውን፣ ይጽደቁ አይጽድቁ ያልታወቀላቸውን የሞቱና ማንነታቸው ያልተረጋገጠላቸውን ሰዎች ስም እየጠሩ መደገስ ማብላት መብላትም ምዕራፍና ቁጥር (መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማስረጃ) የሌለው ደካም ነው።
ክፍል አምስት
ቅዱሳን መላእክትስ ያማልዳሉን?
መላእክት፣ ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደ ሰው ለአገልግሎት የሚላኩ እንጂ ከሰው ወደ እግዚአብሔር ለምልጃ የሚላኩ አይደሉም (ዘካርያስ 110)፡፡ በዕብራውያን 114 ላይ መላእክት «ሁሉ መዳንን ይወርሱ ዘንድ ስላላቸው ለማገዝ የሚላኩ የሚያገለግሉም መናፍስት…» ናቸው በማለት የተፈጠሩበትን መለኮታዊ ዓላማ በግልጽ ይነግረናል፡፡ ለምሳሌ፡- በሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ 10 እና 11 ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደ መቶ አለቃ ቆርኔሌዎስ የተላከው መልአክ፣ መቶ አለቃው ከቤተሰዎቹ ጭምር የሚድንበትን መንገድ የሚነግረውን ጴጥሮስን ከስምዖን ቤት እንዲያስጠራው በመንገር ሰዎቹ ወደ መዳን እንዲደርሱ ማገዙን እናያለን፡፡ ፊልጶስንም እንዲያግዝ የተላከው መልአክ፣ ፊልጶስ ወንጌልን ለኢትዮጵያዊው ጃንደረባ እንዲያደርስ፣ ረድቶአል (ሐዋርያት ሥራ 826-39)
በማቴዎስ 1341 እንደተጻፈው መላእክት ከእግዚአብሔር የሚላኩ ስለሆኑ፡- በዳንኤል 325 መልአክ መምጣቱን ተናግሮ በቁጥር 28 እግዚአብሔር «መልአኩን ልኮ» እንዳዳናቸው እናነባለን፡፡ በዘፍጥረት 167 ከእግዚአብሔር የተላከ መልአክ ወደ አጋር መጣ፤ ነገር ግን አጋር ጠርታው አልነበረም፡፡ በዘፍጥረት 1913 «…እናጠፋውም ዘንድ እግዚአብሔር ሰድዶናል» የሚሉ መላእክት ወደ ሎጥ መጡ እንጂ ሎጥ አልጠራቸውም (ዘፍጥረት 4815)፡፡ እንዲሁም ዮሐንስ 2011 ዳንኤል 1021 1ነገሥት 195 ማቴዎስ 1810 ሉቃስ 126-28 ሐዋርያት ሥራ 126-11 ዘፍጥረት 321-2 መመልከት ይቻላል፡፡
ሰው እግዚአብሔርን በመፍራት የሚኖር ከሆነ የሚጠብቁት መላእክት እንደሚላኩለት በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ በግልጽ ተጽፎ ይገኛል (መዝሙር 347)፡፡ እንዲሁም «ከነዚህ ከታናናሾቹ አንዱን እንዳትንቁ ተጠንቀቁ፤ መላእክቶቻቸው በሰማያት ዘወትር በሰማያት ያለውን የአባቴን  ፊት ያያሉ እላችኋለሁና።» በማለት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በማቴዎስ 1810 ተናግሮአል።  ነገር ግን መላእክት ያማልዳሉ የሚል ትምህርት በቃዱስ ቃሉ ውስጥ ተጽፎ ባለመገኘቱ ምክንያት ፈጽሞ መጽሐፍ ቅዱሳዊ አይደለም፡፡

መላእክት ይቅርታን ከእግዚአብሔር የሚያስገኙና ስለ ኃጢአተኛ የሚማልዱ ሳይሆኑ ለተለያየ አገልግሎት ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደ ሰው የሚላኩ ናቸው፡፡
እምነት ፍጽም በሆነው በአንድ አምላክ በቃ። እርሱ «እነሆ፥ በባሪያዎቹ አይታመንም፤ መላእክቱንም ስንፍና ይከስሳቸዋል» ይላል (ኢዮብ 418) «ደግሞም  እነሆ፥ በቅዱሳኑ ስንኳ አይታመንም፤ ሰማያትም በፊቱ ንጹሐን አይደሉም።» ተብሎ መጻፉን ልብ ካልን (ኢዮ.1515) በቂ መልስ እናገኛለን።
እንዲያውም መላእክት ኃጢአት የሚሠራን ሰው ይቅር የማይሉ ስለሆኑ «በመንገድ ይጠብቅህ ዘንድ ወዳዘጋጀሁትም ስፍራ ያገባህ ዘንድ፣ እነሆ፣ እኔ መልአክን በፊትህ እሰድዳለሁ፡፡ በፊቱ ተጠንቀቁ፣ ቃሉንም አድምጡ፤ ስሜም በእርሱ ስለ ሆነ ኃጢአት ብትሠሩ ይቅር አይልምና አታስመርሩት» (ዘጸአት 2320-21) ተብሎ ተጽፎአል፡፡
በተጨማሪም መላእክት ልመናም ሆነ ስግደት አይቀበሉም፡፡ ሊለመንና ሊሰገድለት የሚገባው አንድ አምላክ ብቻ ነው፡፡ (በማቴዎስ 410 ለሰይጣን የተባለውን ይመልከቱ)፡፡
ስለ መላእክት በራእይ 1910 ሐዋርያው ዮሐንስ ሲጽፍ «ልሰግድለትም በእግሩ ፊት ተደፋሁ፡፡ እርሱም፡- እንዳታደርገው ተጠንቀቅ፤ ከአንተ ጋር የኢየሱስም ምስክር ካላቸው ከወንድሞችህ ጋር አብሬ ባሪያ ነኝ፤ ለእግዚአብሔር ስገድአለኝ» ካለ በኋላ በራእይ 228-9 ደግሞ «ይህንም ያየሁትና የሰማሁት እኔ ዮሐንስ ነኝ፡፡ በሰማሁትና ባየሁትም ጊዜ ይህን ባሳየኝ በመልአኩ እግር ፊት እሰግድ ዘንድ ተደፋሁ፡፡ እርሱም፡- እንዳታደርገው ተጠንቀቅ፤ ከአንተ ጋር ከወንድሞችህም ከነቢያት ጋር የዚህንም መጽሐፍ ቃል ከሚጠብቁ ጋር አብሬ ባሪያ ነኝ፤ ለእግዚአብሔር ስገድ አለኝ» ብሎ ለመላእክት ስግደት እንደማይገባ እውነተኛ የእግዚአብሔር መልአክ በግልጽ አስተማረ፤ ለአንድ አምላክ ብቻ መስገድ ይገባልና! በዚህ ቅዱስ ቃል መሰረት «አማልዳለሁ» እያለ ስግደት የሚፈልግ መልአክ ቢገኝ ለሐዋርያው ዮሐንስ ከተናገረው የእግዚአብሔር መልአክ የተለየና 2ቆሮ. 1114 መሰረት ጽድቅ ፈላጊን ሁሉ ለማሳሳት ራሱን የብርሃን መልአክ አስመስሎ የለወጠና በቅዱሳን መላእክት ስም የሚነግድ ሰይጣን መሆኑን ማስተዋል ይገባል።
በዘካርያስ 112-13 «የእግዚአብሔርም መልአክ መልሶ፡- አቤቱ፣ የሠራዊት ጌታ ሆይ፣ እነዚህ ሰባ ዓመት የተቈጣሃቸውን ኢየሩሳሌምንና የይሁዳን ከተሞች የማትምራቸው እስከ መቼ ነው? አለ፡፡ እግዚአብሔርም መልሶ ከእኔ ጋር ይነጋገር ለነበረው መልአክ በመልካምና በሚያጽናና ቃል ተናገረው» የሚለውን ይህን ጥቅስ «መላእክት ያማልዳሉ» ለማለት አንዳንድ ሰዎች ሲጠቅሱት ይስተዋላል፡፡ በመጀመሪያ መልአኩ ለእግዚአብሔር የራሱን ጥያቄ አቀረበ እንጂ ዘካርያስ «ጠይቅልኝ» ብሎት እንዳይደለ ማስተዋሉ ይበጃል፡፡ ይህ ክፍል መልአኩ «እስከ መቼ ነውብሎ መጠየቁን ነው የሚያሳየን። መላእክት አማላጆች ናቸው የሚል ትምህርት ስህተት የሚሆነው መጽሐፍ ቅዱስ በአንድም ቦታ «መላእክት ያማልዳሉ» የሚል ቃልም ሆነ ይህንን የሚደግፍ ሃሳብ ስለሌለው ነው፡፡ በሌላ አነጋገር ስለ መላእክት አማላጅነት በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ መንገድ የተገለጸ ትምህርት በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አይገኝም፡፡ «መላእክት ያማልዳሉ» ብለው ለሚያስቡ ሰዎች ሃሳባቸው ስህተት የሚሆነው መላእክት ከእግዚአብሔር ወደ ሰው ተልከው የእግዚአብሔርን ሃሳብ ሲያከናውኑ እንጂ አንድም ቦታ እንኳ ሰዎች መላእክትን እንዲህ ብላችሁ ለእግዚአብሔር ችግራችንን ንገሩና መፍትሄ አምጡልን ወይም ጥያቄአችንን አቅሩቡልን ብለው ልመናቸው ቀርቦ ከእግዚአብሔር ዘንድ መልስ ሲስጣቸው በቅዱስ ቃሉ ስላልታየ ነው።
ስለዚህ ለቃሉ ክብርን የሚሰጥ ሁሉ ከተጻፈው ላለማለፍና በሕያው አምላክ ፊት ላለማፈር እንደ ሕያው ቃሉ እውነተኛውን አምላክ ብቻ ማምለክንና ለእርሱም መስገድን ይመርጣል፡፡ እንደ እነዳንኤል በጽድቅ መንገድ ለሚሄዱ ሁሉ መላእክት ተልከው ይመጣሉ፡፡ ዳንኤልም እንዲህ አለ፣ «ገናም በጸሎት ስናገር አስቀድሜ በራእይ አይቼው የነበረው ሰው ገብርኤል እነሆ እየበረረ መጣ፤ በማታም መሥዋዕት ጊዜ ዳሰሰኝ» (ዳንኤል 921) አለ፡፡ በዳንኤል 1012 ደግሞ «እርሱም እንዲህ አለኝ፡- ዳንኤል ሆይ፣ አትፍራ፤ ልብህ ያስተውል ዘንድ፣ ሰውነትህም በአምላክህ ፊት ይዋረድ ዘንድ ካደረግህበት ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ ቃልህ ተሰምቶአል፤ እኔም ስለ ቃልህ መጥቻለሁ፡፡ የፋርስ መንግሥት አለቃ ግን ሀያ አንድ ቀን ተቋቋመኝ፤ እነሆም፣ ከዋነኞቹ አለቆች አንዱ ሚካኤል ሊረዳኝ መጣ፤ እኔም ከፋርስ ነገሥታት ጋር በዚያ ተውሁት» ስለሚል መላእክት ተልከው እኛ ወዳለንበት ለመድረስ ረጅም ጊዜ ሊወስድባቸውም እንደሚችል ማሰቡ እጅግ ጠቃሚ ነው፡፡
ምክንያቱም ብዙ ጽድቅ ፈላጊ ሰዎች «እኛ ኃጢአተኞችና ከእግዚአብሔር እጅግ የራቅን ስለሆንን በቀጥታ ወደ እግዚአብሔር መቅረብ ስለማንችል ፈጥነው በመስማት ምልጃን የሚያከናውኑልን መላእክት ሳይሆኑ አይቀርም» በሚል የዋህነትና መጽሐፍ ቅዱሳዊ ባልሆነ አመለካከት ይታለላሉ።
ይሁን እንጂ ሁልጊዜም ፈጥኖ የሚደርስና የሚረዳ ፈጣሪ ብቻ ነውና «እግዚአብሔር በመካከልዋ ነው አትናወጥም፣ እግዚአብሔርም ፈጥኖ ይረዳታል» ይላል (ማቴዎስ 1128 ፊልጵስዩስ 45 ኤርምያስ 2323 መዝሙር 465 በትኩረት ይመልከቱት)፡፡ ዳንኤል ያለውን ተመልሶ በትኩረት መመልከቱም መንገዳችንን ለማቅናት የበለጠ ይጠቅመናል፡፡
ክፍል ስድስት
ማጠቃለያ
ሕያውና ቅዱስ ቃሉእምነትህ በእግዚአብሔር ይሆን ዘንድ ለአንተ ዛሬ እነሆ አስታወቅሁህ። የእውነትን ቃል እርግጥነት አስታውቅህ ዘንድ፥ ለሚጠይቅህም እውነትን ቃል መመለስ ይቻልህ ዘንድ፥ በምክርና በእውቀት የከበረን ነገር አልጻፍሁልህምን?” (ምሳሌ 2219-21) ስለሚል መጽሐፍ ቅዱስ የመሰከረላቸው ቅዱሳንከተጻፈው አትለፍ የሚለውን በእኛ ትማሩ ዘንድ፥ ይህን በእናንተ ምክንያት ስለ ራሴና ስለ አጵሎስ እንደ ምሳሌ ተናገርሁ።ብለው የመከሩንን መለኮታዊ ምክር አሜን የምንል ከሆንን፣ «የጻድቃን ሰማዕታትንና የመላእክትን አማላጅነት» የሚያስተምር የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ፈጽሞ የለምና መነሻውን የእግዚአብሔር ቃል ያላደረገ መንገድ /ትምህርት/ መጨረሻው ምን እንዲሆን ተገንዝቦ መንገድን ማስተካከል አማራጭ የሌለው መልካም እርምጃ ይሆናል።
ታዲያ መጽሐፍ ቅዱስ የማያውቀው ትምህርት የማን ነው ትላላችሁ? የክርስቶስን ክቡር ደም በመስቀል ላይ መፍሰስ ትርጉም የለሽ ለማድረግ በጠላት በተፈጠረ /በተፈለሰፈ/ እና መጽሐፍ ቅዱሳዊ ባልሆነ ሰው-ሠራሽ ትምህርት ምክንያት ከተከሰቱ ታላላቅ ስህተቶች መካከል፡- አንደኛው እግዚአብሔር «እኔ የቅርብ አምላክ ነኝ» ብሎ እየተናገረ እያለ ከሰው እጅግ ርቆ የሚኖር የማይሰማና የማያይ አምላክ ማድረግ፡፡ እንዲሁም ዳዊት በመዝሙሩ 1397 «ከመንፈስህ ወዴት እሄዳለሁ? ከፊትህስ ወደ ማን እሸሻለሁብሎ ሁሉ ቦታ የሚገኝ መሆኑን የተናገረለትን አምላክ ከሰው እጅግ ርቆ የሚኖር እንጂ በሁሉ ስፍራ የማይገኝ ማድረግ የመጀመሪያው ስሕተት ነው።
ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩትን ሰዎችና በቦታና በጊዜ ውስን የሆኑትን መላእክት (ፍጡራንን) እንደ ፈጣሪ በሁሉም ሥፍራ የሚገኙ አድርጎ የፈጣሪን ቦታ ለመስጠት ማሰብና ማመን መለመንም እግዚአብሔር ራሱ ጻድቃን ሰማዕታትና ቅዱሳን መልእክትም ሁሉ የሚቃወሙት እና የሚጸየፉት ሁለተኛው ስህተት ነው፡፡ (ኢሳይያስ 111-17 661-4 መሳፍንት 1315-16 ራእይ 228-9 የሐዋ.ሥራ 1411-18 ሉቃስ 1619-31 ዮሐንስ 21-11)
የእግዚአብሔር ቃል ከዘፍጥረት እስከ ራእይ ዮሐንስ ቢመረመር አንድም ሰው እንኳን ጻድቃን ሰማዕታትን ወይም መላእክትንአማልዱኝብሎ የጸለየ እንደሌለ እውነትንና ጽድቅን ፈላጊ ሁሉ ሊያውቀውና ልብም ሊለው ይገባል፡፡ በቀራንዮ በመስቀል ላይ የፈሰሰው ክቡር የክርስቶስ ደም ኃጢአተኛን ሰው ከአምላኩ ጋር ለማስታረቅ አስተማማኝነቱ ከዕልፍ-አዕላፍት መላእክትም ሆነ ከሥጋ ለባሽ ሁሉ ምልጃ እጅግ ይበልጣል (ዕብራውያን 1029 725)፡፡
የዓለም መድሃኒት የሆነው ጌታችንና መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ፦እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፥ ወደ እኔ ኑ፥ እኔም አሳርፋችኋለሁ። ቀንበሬን በላያችሁ ተሸከሙ ከእኔም ተማሩ፥ እኔ የዋህ በልቤም ትሑት ነኝና፥ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ፤ ቀንበሬ ልዝብ ሸክሜም ቀሊል ነውናብሎ ይጣራልና ወደ እርሱ መቅረብ ብቻ ይበጃል። 1ዮሐንስ 17-9 ለኃጢአት ይቅርታ የክርስቶስ ደም በቂ ሆኖ ሳለ ፍጡራንን «…ይቅርታን ለምኝልንለምንልን…» ማለት እንድ እግዚአብሔር ቃል ሲታይ ተገቢ አይደለም።
በዮሐንስ 1414 መሠረት ለጥያቄ ሁሉ የኢየሱስ ስም መልስ የሚያስገኝ ሆኖ ሳለ በሌላ ስም የጸሎት መልስ ለማግኘት ጥረት ማድረግ መጽሐፍ ቅዱሳዊ አይደለም።